Liyu🌸 · @liyuandkidus

Posted 4 days ago
1.02M followers
250.5K views
29.3K likes
314 comments
320 shares

የኔ ኤልናታን ❤️ አንተ ለኔ ሕይወት አስቀጠልክልኝ። የኔ ወርቅ ልጅ፣ አንተን ሳረግዝ አምላኬን አየሁ። በሆዴ ውስጥ ሳስብህ ተስፋ ተሰማኝ፣ ልቤም በፍቅር ተሞላ። አንተን ስወልድ ብዙ ተፈተንኩኝ፣ ብዙ አለቀስኩ፣ ብዙ አመመኝ… ግን መድኃኔዓለም ቸር ነው፤ ፈተነኝ እንጂ አልተወኝም። አንተን አቅፌ በያዝኩህ ቀን ግን ሁሉንም ህመም ረሳሁት። የኔ ልጅ፣ ባንተ ምክንያት “እናት” ተባልኩ። ባንተ ምክንያት ሕይወቴ ትርጉም አገኘች። አንተ የኔ ጥንካሬ፣ የኔ ደስታ፣ የኔ ሰላም ነህ። በደከመኝ ቀን ፈገግታህ ያበረታታኛል፤ ልቤ ሲሰበር ድምፅህ ያነሳኛል። የኔ ዓለም ልጄ፣ ሕይወቴ ባንተ ተባረከች። እግዚአብሔር ከሰጠኝ ታላቅ ስጦታ ሁሉ በላይ አንተ ነህ። እንኳን ወለድኩህ፤ እንኳን የኔ ሆንክ። የኔ ወርቅ፣ የኔ ኤልናታን፣ እወድሃለሁ። ትልቅ ሰው ሆነህ እንዳይለይህ ፍቅሬ ሁሌም ካንተ ጋር ነው። እናት ለአንተ ሁሉንም ትሆናለች፣ ሁሌም ትጠብቅሃለች፣ ሁሌም ትወድሃለች። ❤️ መልካም የእናቶች ቀን ለኔ… ምክንያቱም አንተ አለህ❤️